2014 በጀት ዓመት የኮርፖሬት ማኃበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር የተከናወኑ ስራዎች(የተከናወነ ካለ ብቻ በሪፖርት የሚካተት)

  • ለቃሊቲ አቃቂ ክፍለ ከተማ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የ2 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ ተከናውኗል፡፡
  • ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ብር 4 ሚሊዮን ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • በአዲስ አበባ መስተዳደር ጥያቄ መሰረት በአካባቢው ለሚኖሩ አንድ አቅመደካማ ነዋሪ የመኖርያ ቤት የመስራት ስራ ተከናውኗል፡፡ በዚህም ድርጅቱ 300 ሺ ብር ወጪ አድርጓል፡፡
  • በድርጅቱ ውስጥ ለሚሰቱ ሴት ሰራተኞ ህጻናት ልጆች ማቆያ ድርጅቱ ያደራጀ ሲሆን ለዚህም በበጀት አመቱ 172800 ብር ወጪ አድርጓል፡፡
  • በአካባቢው ለሚገኙ ለጥበቃ አባላት 6 ሺ ብር የሚያወጣ አንጸባራቂ እና ሴፍቲ ጫማ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • ከደመወዝ ላይ ተቆራጭ የሚደረግ እና በድርጅቱ ውስት በኤች አይ ቪ ኤድስ የተያዙ ሰራተኞች ለመደገፍ 19,2ዐዐ ተሰብስቦ ለማህበሩ ገቢ ተደርጓል
  • ለሃገር መከላከያ እና በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የአንድ ወር ደመወዝ 2500000 ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • በአካባቢው ለሚኖሩ ማህበረሰብ አካላት ግምቱ 100 ሺ ብር የሚሆን የማገዶ እንጨት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • እህት ኩባንያ በሆነው በዋንዛ ፈርኒቸር በኩል ለትምህርት ቤት ለሚሆን ወንበርና ጠረጸዛ ክፍያ የሚኖን ብር 817,580.00 ወጪ ተደርጓል፡፡

News